Dawit Mengiste Legal Services

Dawit Mengiste is a licensed business and criminal lawyer based in Addis Ababa, Ethiopia.

Having graduated with LLM in Business Law from Addis Ababa University and worked as a Federal Public Prosecutor at the FDRE Ministry of Justice, Dawit Mengiste has been practicing law in different areas for the last Forteen years.

Besides his advisory and attorneyship services, Dawit Mengiste also conducts legal research. He published one Amharic book and a number of articles.      

officer

Legal Updates

የአደጋ ጊዜ መኪኖች የመንገድ አጠቃቀም ከሕግ አንጻር እንዴት ይታያል?

በአዲስ አበባ ዋና ዋና መንገዶች ላይ ስንንቀሳቀስ ልብ ማለት እንደምንችለው የአምቡላንስ፣ የፖሊስ፣ የመከላከያ እና የእሳት አደጋ መኪኖች አሽከርካሪዎች ከመንገድ ትራፊክ ሕጎች በተቃራኒ ያሽከረክራሉ እንዲሁም የትራፊክ ተቆጣጣሪዎችም የእነዚህ መኪኖች አሽከርካሪዎች ከመንገድ ትራፊክ ሕጎች በተቃራኒ እንዲያሽከረክሩ ይፈቅዱላቸዋል፡፡  

በሌላ በኩል ሁሉም የመንገድ ተጠቃሚ የመንገድ ትራፊክ ሕጎችን አክብሮና ጠብቆ እንዲያሽከረክር የሕግ ግዴታ እንዳለበት ይታወቃል፡፡

ከዚህ አንፃር ይህ የሕግ አፕዴት የመንገድ ትራፊክ ሕጎችን በመመርመር የአምቡላንስ፣ የፖሊስ፣ የመከላከያ እና የእሳት አደጋ መኪኖች አሽከርካሪዎች ከመንገድ ትራፊክ ሕጎች በተቃራኒ የማሽከርከራቸውን ወይም የትራፊክ ተቆጣጣሪዎች እነዚህ አሽከርካሪዎች በዚህ መልኩ እንዲያሽከረክሩ የመፍቀዳቸውን ተገቢነት ያስነብባል፡፡

 

ያለመያዣ ለሚደረግ የብድር ውል የሚከፈለው የቴምብር ቀረጥ አምስት ብር ብቻ ስለመሆኑ

የፌዴራል የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ከሚያስከፍላቸው ክፍያዎች ውስጥ አንዱ የቴምብር ቀረጥ ነው፡፡ የቴምብር ቀረጥ ራሱን የቻለ የግብር አይነት ሲሆን የሚከፈለውም በቴምብር ቀረጥ አዋጅ ቁጥር 110/1990 መሠረት ነው፡፡

በዚህ አዋጅ ላይ የቴምብር ቀረጥ የግድ ሊከፈልባቸው የሚገባ ሰነዶች ተለይተው የተጠቀሱ በመሆኑ የፌዴራል የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎትም የቴምብር ቀረጥ ክፍያ ሊጠይቅ የሚገባው ወይም የሚችለው አዋጁን በመከተል ብቻ ነው፡፡

ይህ የሕግ አፕዴት የፌዴራል የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት በተግባር እንደሚስተዋለው ያለመያዣ ለሚደረግ የብድር ውል የብድር መጠኑን አንድ በመቶ የቴምብር ቀረጥ እንዲከፈልበት የማድረጉን ተገቢነት ከአዋጁ አኳያ በመመርመር ተገቢ አለመሆኑን የሚያስረዳ ነው፡፡   

የሪል እስቴት አልሚዎች በአዲሱ ሕግ መሠረት ለውጭ አገር ዜጎች ቤት ሲሸጡ ሊያውቋቸው የሚገቡ ነጥቦች

የውጭ አገር ዜጎች በኢትዮጵያ ውስጥ የቤት ባለቤት ለመሆን እንዳይችሉ ከ1953 ዓ.ም ጀምሮ ተጥሎ የቆየ የሕግ ክልከላ በመኖሩ ምክንያት በአገራችን የሚንቀሳቀሱ የሪል እስቴት አልሚዎችም የሚገነቧቸውን ቤቶች ለውጭ አገር ዜጎች ለመሸጥ ሳይችሉ ቆይተዋል፡፡  

ከመስከረም 22 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ሥራ የገባውንና የውጭ አገር ዜጎች በኢትዮጵያ ውስጥ የቤት ባለቤት ለመሆን እንዲችሉ የፈቀደውን አዋጅ ቁጥር 1388/2017 ተከትሎ ግን የአገራችን የሪል እስቴት አልሚዎች አንድ ጥሩ የገበያ አማራጭ እንደሚፈጠርላቸው መገመት ይቻላል፡፡

ምንም እንኳን የዚህ አዋጅ መምጣት ለአገራችን የሪል እስቴት አልሚዎች ጥሩ የገበያ አማራጭ እንደሚፈጥርላቸው ቢገመትም አዋጁ ያስቀመጣቸውን ልዩ ልዩ ሁኔታዎች በሚገባ መገንዘብ ግን የግድ ይላል፡፡

ስለሆነም ይህ ሌጋል አፕዴት ለውጭ አገር ዜጎች ቤት ከሚሸጡ የሪል እስቴት አልሚዎች አንፃር አዲሱ አዋጅ ምን ቁልፍ ጉዳዮችን ይዟል የሚለውን ጥያቄ ይመልሳል፡፡  

Formation of Holding Companies in Ethiopia

As one form of business organization, Holding Company is a well-developed concept in most jurisdictions. However, it is a very recent introduction to the Ethiopian legal system.

The major legal instruments in Ethiopia regarding Holding Companies are the Commercial Registration and Licensing Proclamation No. 980/2016 (together with its Amendment, and Implementing Regulation and Directive) and the Commercial Code of Ethiopia Proclamation No. 1243/2021.

Among the different issues regulated under these legal instruments, this Legal Update briefly shows how Holding Companies can be formed in Ethiopia.

How Foreign Businesses Can Open their Branches and Make Business in Ethiopia?

Obviously, there are a number of Foreign Businessmen and Business Organizations that are already doing business in Ethiopia through their Branches. In fact, there can also be others intending to open Branches and carry on Business.

Thus, it is relevant to show the legal requirements for Foreign Businessmen and Business Organizations to open their Branches and make business in Ethiopia.

This Legal Update discusses the legal requirements in this regard.